Filtra per genere

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

4236 - "ሎሬየት ፀጋዬ ገ/መድኅን የሀገር ዋርካ የሆነ አይተኬ ድንቅ የፈጠራ ሰው ነው፤ እንደ ፀጋዬ ያለ ሰው በምዕተ ዓመት ውስጥ የሚፈጠረው አንዴ ነው" አበራ ለማ
0:00 / 0:00
1x
  • 4236 - "ሎሬየት ፀጋዬ ገ/መድኅን የሀገር ዋርካ የሆነ አይተኬ ድንቅ የፈጠራ ሰው ነው፤ እንደ ፀጋዬ ያለ ሰው በምዕተ ዓመት ውስጥ የሚፈጠረው አንዴ ነው" አበራ ለማ

    ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ተዘፍኖ ዘመን ተሻጋሪ ስለ ሆነው "ሀገሬን አትንኳት" ግጥሙ፣ ስለ ባለ ቅኔ ሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ዘርፈ ብዙ ተጠባቢነትና ወዳጅነት አንስቶ ይናገራል። ሥነ ግጥሞቹንም ያስደምጣል።

    Sat, 04 May 2024 - 17min
  • 4235 - "ሥነ ፅሑፍ ቁራኛ ነው፤ ከፀሐፊው ጋር በፍቅርም በትንቅንቅም ተያይዘው ይዘልቃሉ፤ አይላቀቁም" ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ

    ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በቅርቡ ለአንባቢያን እነሆኝ ስላለው "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉና የሥነ ግጥም በረከቶቹ ይናገራል።

    Sat, 04 May 2024 - 18min
  • 4234 - "ጋዜጠኛ በንፁህ ኅሊናው ሚዛናዊ የጋዜጠኛነት ሥራን መሥራት እንጂ፤ ሙያውን የሚያራክስ ነገር መሥራት የለበትም። አሁን እንደወረርሽኝ የወረረን እሱ ነው" አበራ ለማ

    ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ የአገረ ኢትዮጵያን የራዲዮ ስርጭት፣ የጋዜጣ ሕትመት ውጤቶችንና የባለ ሙያዎቹን የሥነ ምግባር ደረጃ መዝኖ ግለ አተያዩን ያጋራል።

    Sat, 04 May 2024 - 14min
  • 4233 - አበራ ለማ፤ ከመምህርነት ወደ ጋዜጠኛነትና ደራሲነት

    ከኢትዮጵያ አንጋፋና ስመ ገነን ጋዜጠኞችና ደራሲዎች ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ከሆኑቱ ውስጥ አበራ ለማ አንዱ ነው። በማስታወቂያ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ራዲዮና አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በግሉ ፕሬስ በአዕምሮ ጋዜጣ የጋዜጠኛነት ድርሻውን አበርክቷል። በድርሰት በረከቶቹም ሰሞነኛውን "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉን አክሎ ከ20 በላይ መፅሐፍትን ለተደራሲያን እነሆኝ ብሏል።

    Fri, 03 May 2024 - 12min
  • 4232 - Understanding the profound connections First Nations have with the land - ነባር ዜጎች ከመሬታቸው ጋር ያላቸውን ጥልቅ ቁርኝቶች መረዳት

    The land holds a profound spiritual significance for Aboriginal and Torres Strait Islander peoples, intricately intertwined with their identity, belonging, and way of life. - ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች መሬት ጥልቅ መንፈሳዊ ፋይዳን የያዘ፣ ከማንነታቸው፣ ውሁድነትና የአኗኗር ዘዬ ጋር ተጋምዶ የተቆራኘ ነው።

    Thu, 02 May 2024 - 07min
Mostra altri episodi